

የልቤ ትርታ
ውዷ የኔ
ፍቅር፣
የልቤ ትርታ፣
ጠረንሽ
ናፈቀኝ እንደ ሎሚ ሽታ። ከጎኔ
ሁኚልኝ ለትንሽ ቆይታ፣ ልቤ እንዳይጨነቅ አንቺን ያጣ ለታ።
አሁንስ አቃተኝ፣ በዛብኝ
ፍቅርሽ፣ ያለሁት ጠፋብኝ
ሲጠራ ስምሽ።
አካሌ ሁሉ ደከመ አቃተኝ ፍቅርሽ፣
እቅፍ አድርጊና ነካኪኝ በእጅሽ።
ውዷ የኔ ፍቅር፣
ናፈቀኝ
አካልሽ፣ ሁሌም ስተኛ
በህልሜ
አቅፍሽ።
ዘወትር የማደንቀው ያ ውዱ ከንፈርሽ፣ ውበትሽን የሚያደምቀው ደማቁ ፈገግታሽ። ሰውን የሚያፈዝዘው ያ
ልዩ ሳቅሽ፣
ከሰው
የሚለይሽ መዓዛው ጠረንሽ። ሁሉም ተደምረው
ነፀብራቁ
አካልሽ፣
ልቤን አፈዘዘው ባንድ ጊዜ ሳይሽ።
ታዲያ ምን አለበት ዘላለም ባፈቅርሽ?
በልቤ ቃል ገባሁ ደግሜ ልወድሽ።
ሁሉም ይፈፀማል ይደመጣል ቃልሽ፣
እኔም እሆናለሁ የወደፊት
ባልሽ። እስከዚያ ድረስ ፈጣሪ ከመጥፎ ይጠብቅሽ
እኔም በፍቅር ሁሌ እጠብቅሻለሁ